የልደቴ ቀን
መስከረም ሰለሞን
መስከረም ሰለሞን

ዛሬ ደስ የሚል ቀን ነው ደስ ያለኝ ደግሞ ልደቴ ስለሆነ ነው ስሜ ልዩ ነው በሂወቴ በጣም ደስ ከሚሉኝ ቀናቶች መካከል አንደኛዉና ዋነኛ ዉ የልደት ቀኔ ነው ምክንያቱም የተወለድኩበት ቀን ስለሆነ ነው። አሁን ቤተሠቦቼ ምን አያደረጉ ይሆን?

1

ልዩ:ጓደኞቼ ሳልነግራችሁ ዛሬኮ የልደቴ ቀን ነው።
ፍቅር:ወይኔ እረስቸው እንኳን ተወለድሽ ጓደኛዬ መልካም ልደት።
ናታን:እንኳን ተወለድሽ ጓደኛችን መልካም ልደት።
ልዩ:አመሰግናለሁ ወደቤት እንሂድ።

2

ሶስቱ ጓደኛሞች በመንገድ ሲሄዱ ምን አይነት ዝግጅት ይሆን የሚዘጋጅልሽ እያሏት ሲሄዱ አንድ ሰው በመኪና መቶ ኑልጋብዛችሁ በማለት ሊሸውዳቸው ሞከረ።እነሱም የተማሩትን በማስታወስ ከማናቀው ሰው ጋር አንሄድም አሉት።እሱም አፍሮ ሄደ እነሱም መንገዳቸውን ቀጠሉ።

3

ቤቷ ከደረሱ ቡኋላ እንደጠበቁት የልደት ዝግጅቱ ተዘጋጅቶ ነበር ።እነሱም በደስታ ዘለሉ በጠረንቤዛው ለይ ኬክ፣ዳቦ እና ፍራፍሬወች ተደርድረዋል ቤተሰቦቼን አመሰገንኩአቸው።

4

ጓደኞቼና ዘመዶቼ ስጦታ ሰጡኝ እናቴ ቀሚስ ገዛችልኝ እናትና አባቴን አቅፌ ሳምኩአቸው ።

5

ጓደኞቼና ዘመዶቼ ከተሰባሰቡ ቡኋላ የልደት ዝግጅቱ ተጀመረ ሁሉም በአንድ ላይ መልካም ልደት እያሉ ዘመሩ።ኬኩ ተቆረሰሻማውን አጠፋሁ ደስ በሚል ሁኔታ አከበርኩ።

6

ዘመዶቼ መረቁኝ የመጡልኝን ስጦታወች ተመለከትኩ በጣም ያማምራሉ አመሰገንኩአቸው።

7

በጣም ደስ የሚል ቀን ነበር አሁን ዝግጅቱ ተጠናቆ ቤተሰቦቼና ጓጀደኞቼ ወደ ቤታቸው ሄዱ።

8

እስከ ዛሬ ካከበርኩአቸው የልደት ቀኔ በይበልጥ ወድጀዋለሁ በጣም ደስየሚል ቀን ነው።የሰባት አመቴ ልደቴ ይሄን ይመስል ነበር ደህና ሁኑ ለጆች።

9
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
የልደቴ ቀን
Author - መስከረም ሰለሞን
Illustration - መስከረም ሰለሞን
Language - Amharic
Level - First paragraphs