ብልሁ ዝንጀሮ እና ሞኞቹ ድመቶች
ናታኒየም ቱሉ
ናታኒየም ቱሉ

ከእለታት አንድ ቀን ሁለት ድመቶች በአንድ ኬክ ይጣሉ ነበር። አንደኛው ድመት "ግማሹን እኔ ልብላ" አለ። ሌላኛው ደግሞ "አይ፣ አይሆንም እኔ ነኝ ግማሹን የምበላው። አንተ ሩቡን ትበላለህ" አለው።

1

በዚህ ጊዜ ሲጣሉ ያየ ዝንጀሮ ወደነሱ መጣና "ከምትጣሉ እኔ እኩል ላካፍላችሁ" አለ። ሁለቱም ድመቶች በሐሳቡ ተስማሙ።

2

ከዚያ በኋላ ኬኩን ከፈለውና "ግማሹ ስለበዛ ልብላለት" አለና ገመጠው። ሁለተኛውን ደግሞ "በዛ" እያለ ሙሉውን ኬክ ጨረሰው።

3

ድመቶቹ ደግሞ ይህንን ሲያዩ ተናደው ሊይዙት ሲሉ ከዛፍ ወደ ዛፍ እየተንጠላጠለ አሹፎባቸው ጥሏቸው ጠፋ። እነሱም ተናደው በራሳቸው ሞኝነት ብዛት የደረሰባቸውን ችግር በማሰብ መከባበር ጀመሩ።

4
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ብልሁ ዝንጀሮ እና ሞኞቹ ድመቶች
Author - ናታኒየም ቱሉ
Illustration - ናታኒየም ቱሉ
Language - Amharic
Level - First paragraphs