ንቦች፣ ታታሪዎቹ ጀግኖች
Nema Behutiye
Mekasha Haile

ንቦች ታታሪ ፍጡራን ናቸው፡፡

1

ንቦች የራሳቸው የሥራ ክፍፍል አላቸው፡፡ ንቦች ንግስት ንብ፣ ወታደሮችና ሠራተኞች ተብለው በሦስት ክፍሎች ይመደባሉ፡፡

2

ወታደር ንቦች የንግስቲቱንና የግዛታቸውን ደህንነት ይጠብቃሉ፡፡

3

የንግስቲቱ ንብ ተግባር እንቁላል መጣል ነው፡፡

4

ሠራተኛ ንቦች ጋራ ሸንተረሩን በማቋረጥና አበባ በመቅሰም ማር ይሠራሉ፡፡

5

የንቦች ትጋትና ኅብረት ለሰዎች ጭምር አርአያነት ያለው ተግባር ነው፡፡

6

ንቦች ጥቃት አይወዱም፡፡ ለምሳሌ አናቢ በጭስ አፍኖ ማር ሲቆርጥ ይከፋቸዋል፡፡

7

ለዚህም ነው ሰዎች ማር ለመቁረጥ ጭስ የሚጠቀሙት፡፡

8

ንቦች ያለ አግባብ ሲደፈሩ ሰውንና እንስሳትን ይነድፋሉ፤ ያባርራሉ፡፡

9

ንቦች ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀሱ በጋራ ነው፡፡

10

ንቦች አትንኩኝ ባይ ናቸው፡፡

11

ንቦች ለሰው ልጅ እጅግ ጠቃሚ የሆነና መድኃኒትነት ያለውን ጣፋጭ ማር ይሠራሉ፡፡

12

ንቦች ለሥራ ሲሰማሩ በዘመቻ መልክ ነው፡፡

13

ንቦች የአርሶአደር አጋሮች ናቸው፡፡

14

ንቦች የተመቻቸ አካባቢን ይወዳሉ፡፡

15
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ንቦች፣ ታታሪዎቹ ጀግኖች
Author - Nema Behutiye
Illustration - Mekasha Haile
Language - Amharic
Level - First sentences