አስገራሚው ጉንዳን
Nema Behutiye
Mekasha Haile

ጉንዳን ከክብደቱ በላይ የሆነ አካልን ይሸከማል፡፡

1

ጉንዳን በማኅበራዊ ኑሮ ረገድ ሰዎችን ያስቀናል፡፡

2

ጉንዳን የተጎዳ ወገኑን በጋራ ጎትቶ ከምሽግ ያደርሳል እንጂ ጥሎ አይሄድም፡፡

3

ጉንዳን ጎርፍ ወይም ወራጅ ውሃ ቢያጋጥመው ወገብ ለወገብ ተያይዞ ይሻገራል እንጂ በዉኃ አይወሰድም፤ በዚህ ምክንያት ከአሰበበት ጉዳይ አይመለስም፡፡

4

ጉንዳን በቀላሉ ለጠላቱ አይበገርም፡፡

5

ጉንዳን የከብት መንጋን ሳይቀር ያሸብራል፡፡

6

ጉንዳን በመተባበር ወፎችን፣ ዶሮዎችንና በረሮዎችን ይገድላል፡፡

7

ጉንዳን ጀግና ሰውን ሳይቀር የያዘውን መሣሪያ ያስጥላል፡፡

8

ጉንዳን ኃያሉን አንበሳ ሳይቀር ይፈታተናል፡፡

9

ጉንዳን እኔ ነኝ ያለን ጎበዝ ውሻንም መድረሻ ያሳጣል፡፡

10

ጉንዳን ዝሆንን ‹‹የት ልግባ?›› ያሰኛል፡፡

11

ጉንዳን ቀንዳሙን ጎሽ ካገኘው ያስጮኸዋል፡፡

12

ጉንዳን እባብን በቀላሉ ይገድላል፡፡

13

ጉንዳን አይጦችን በቀላሉ ያጠቃል፡፡

14

ጉንዳን አያ ጅቦን ሳይቀር ጉያው ሥር በመግባት ያስጮኸዋል፡፡

15

ጉንዳን ከርከሮን ያስጨንቃል፡፡

16

ጉንዳን ጥንቸልን ካገኘ ያስሮጣታል፡፡

17

ጉንዳን ድንጋይ ለበሷንና ቀርፋፋዋን ኤሊን ፍጥነት ያስጨምራታል፡፡

18

ጉንዳን ድመትን መግቢያ ቀዳዳ ያሳጣል፡፡

19

ጉንዳን ፍየልን ያዘልላታል፡፡

20

ጉንዳን ሴትን ያስጮሃል፤ ያስሮጣል፡፡

21

ጉንዳን ወንድን ያስዘልላል፡፡

22

ጉንዳን ርግቦችን ያራውጣል፡፡

23

ጉንዳን ታታሪዋን ንብ ያጠቃል፡፡

24

ሆኖም ጉንዳን አጃክስን፣ ነጭ ባህር ዛፍን፣ ጋዝና ሽታ ያላቸውን ኬሚካሎችን ይፈራል፤

25

ጉንዳን በፈላ ውሃ ድምጥማጡ ይጠፋል፡፡

26
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
አስገራሚው ጉንዳን
Author - Nema Behutiye
Illustration - Mekasha Haile
Language - Amharic
Level - First sentences