ክንፍ ያበቀለው ልጅ
Worku Debele
Tadesse Teshome

በድሮ ጊዜ ሁለት ወንድ ልጆች ያሏቸው አንድ ሀብታም ሰው ነበሩ፡፡ ሀብታሙም ሰውዬ በኑዛዜያቸው ላይ የበኩር ልጃቸው ሁሉንም ላሞቻቸውን እንዲወስድ ተናዘዙለት፡፡ ለትንሹ ልጃቸው ግን አንድ አውራ ዶሮ ብቻ ተናዘዙ፡፡

1

ሰውዬውም ከሞቱ በኋላ የበኩር ልጃቸው ሁሉንም ላሞች ወሰደ፡፡ ትንሹ ልጅ ግን አንድ አውራ ዶሮ ብቻ ደረሰው፡፡

2

ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ሀብታሙ ልጅ ታመመ፡፡ መፍትሔ ፍለጋም ወደ አንድ የባሕል መድሐኒት አዋቂ ሰው ሄደ፡፡ መድሐኒት አዋቂውም ''አንዲህ እንዲህ ዓይነት አውራ ዶሮ እረድ'' አሉት፡፡

3

ሀብታሙም ልጅ የተባለውን ዓይነት አውራ ዶሮ ለማግኘት ተቸገረ፡፡ ከዚያም የወንድሙን አውራ ዶሮ አስታወሰ፡፡ ወደ ወንድሙም የተወሰኑ ሰዎችን ላከ፡፡

4

ወንድምዬውም ''ያለኝ አንድ ብቸኛ ሀብት ይሄ አውራ ዶሮ ነው፡፡ ወንድሜን ካዳነው ግን ከወንድሜ ስለማይበልጥብኝ ሰጥቻለሁ'' አላቸው፡፡

5

ሰዎቹ ዶሮውን አርደው ለታመመው ልጅ አበሉት፡፡ ልጁም ከሕመሙ ዳነ፡፡

6

ከተወሰነ ጊዜ በኋላም እጅግ ያልተለመደ ነገር ተከሰተ፡፡ የሀብታሙ ልጅ ሰውነት ላባና ክንፎች ማብቀል ጀመረ፡፡

7

የሚያየውን ማመን አልቻለም፡፡

8

ወደ አዛውንቶች ሄደ፡፡ እነሱም ''ይህ ወንድምህን ስለበደልከው የመጣብህ ቁጣ ነው፡፡ ሁሉንም ላሞች ወስደህ ስታበቃ፤ አባትህ ያወረሱትን ዶሮም በላህበት!'' አሉት፡፡ ሽማግሌዎቹ ለሀብታሙ ልጅ ''እንድትድን ከፈለግህ ወንድምህ ይቅር ሊልህ ይገባል'' አሉት፡፡

9

ሽማግሌዎቹ ''ይህን የእጅ አምባር የምህረቱ ምልክት እንዲሆን ለወንድምህ እንሰጠዋን፡፡ ከተፋበት ትድናለህ'' ሲሉ አስረዱት፡፡

10

ሽማግሌዎቹም የእጅ አምባሩን ወንድሙ ጋ ወስደው ''ትፋበትና ወንድምህን ይቅር በለው'' አሉት፡፡ ወንድምዬውም ተፋበት፡፡

11

በመሆኑም ሽማግሌዎቹ ከሀብታሙ ልጅ ላሞች ግማሹን ለድሃው ወንድሙ ለመስጠት ወሰኑ፡፡

12
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ክንፍ ያበቀለው ልጅ
Author - Worku Debele, Elizabeth Laird
Translation - መዘምር ግርማ
Illustration - Tadesse Teshome
Language - Amharic
Level - First paragraphs