ነብርና አይጥ
Abdulkadir Guracha
Rob Owen

በድሮ ጊዜ ነብርና አይጥ ጓደኛሞች ነበሩ፡፡ የጋራ ፍየሎችም ነበሯቸው፡፡ እነዚያን ፍየሎች ለማገድም ተራ ገብተው ነበር፡፡

1

ነብር ጎበዝ እረኛ የሚባል አልነበረም፡፡ ፍየሎቹን ባሰማራቸው ቁጥር ተርበው ይመጣሉ፡፡

2

አይጧ ሁልጊዜ ከእናቷ ጋር ነበር የምትወጣው፡፡ የአይጧ እናት ዛፍ ላይ ትወጣና ቅጠሎችን ትለመልማለች፡፡ ለፍየሎቹም ትወረውልላቸውና በደስታ ይበላሉ፡፡

3

አንድ ቀን ነብር ለአይጥ ''ፍየሎቹ አንቺ ስታሰማሪያቸው ወደ ቤት በደስታ ይመጣሉ፡፡ እኔ ሳሰማራቸው ግን ተርበው ነው የሚመጡት፡፡ ለመሆኑ ምክንያቱ ምንድነው?'' አላት፡፡ አይጧም እሳቱ አጠገብ ወዳለው የከብት መተኮሻ ብረት ጠቆመች፡፡

4

''ያንን መተኮሻ ብረት ፍየሎቹ ጭራ ላይ አስረዋለሁ፡፡ ይፈሩና ሲሯሯጡ የሚበላ ነገር ያገኛሉ፡፡ አንተ ስታግድ ግን የትም ሳይሄዱ አንድ ቦታ ይቀመጣሉ፡፡ ምግብ የማያገኙትም ለዚያ ነው'' ትለዋለች፡፡.

5

ነብሩ ተናደደ፡፡ ''ይቺ ደንቆሮ አይጥ እውነቱን አልነገረችኝም'' በማለት አሰበ፡፡ እየቀለደችብኝ ነው፡፡ ነገ ጠዋት ተከትያት እሄድና ጉዷን አያለሁ''  አለ፡፡

6

በቀጣዩም ቀን ነብር እንዳሰበው አይጧን ተከተላት፡፡ እንዳታየውም ጥንቃቄ አድርጓል፡፡ ከሩቅም ያያት ጀመር፡፡

7

አይጧም ዛፍ ስር ቆማ ''እማማ! ነይ አግዢኝ! ለፍየሎቼ የሚበላ ያስፈልገኛል!'' አለች፡፡ ወዲያውኑም የአይጧ እናት ልጇን ታግዛት ጀመር፡፡ ቅጠሎቹን ለመለመችላት፡፡

8

''እውብኝ እስቲ!'' አለ ነብር፡፡ አይጧ እናቷ እያገዘቻት ነው ለካ፡፡ ምንም አይነት መተኮሻ ብረት አልተጠቀመችም'' ሲል ተናደደ፡፡ ''አይጧ እኔን ቂል አድርጋኛለች'' ሲል አሰበ፡፡ ''ልታታልዪኝ! እ! ቆይ ግን አሳይሻለሁ!'' አለ፡፡.

9

በማግስቱ ፍየል የማገዱ ተራ የነብር ነበር፡፡ ፍየሎቹን ዛፉን አሳልፎ አቆመና ''እማማ! ነይ እርጂኝ! ለፍየሎቼ  የሚበላ አፋልጊኝ'' አለ፡፡ የአይጧ እናት ከዛፉ ሮጣ ስትወርድ ነብሩ ዘለለና ቁብ አለባት፡፡ አንቆም ገደላት፡፡

10

በቀጣዩ ቀን የአይጥ ተራ ነበር፡፡ ፍየሎቹን ዛፉን አሳልፋ ወሰደችና ''እማማ! ነይ እርጂኝ! ለፍየሎቼ የሚበላ አውርጂልኝ'' አለቻት፡፡ ይሁን እንጂ ምንም ምላሽ አላገኘችም፡፡ እናቷም አልመጣችላት፡፡ አይጧ እንደገና ''እማማ!'' ስትል ተጣራች፡፡ የት ነው ያለሽው እማዬ?''

11

አይጥ ተጠራጥራ ማልቀስ ጀመረች፡፡ ''ወይኔ እናታለም'' በማለት አነባች፡፡ ''ሞተሻል፡፡ ነብሩ ነው የገደለሽ?'' አይጢት ሙሉ ቀን ስታቅስ ስለዋለች ዓይኖቿ በርበሬ መሰሉ፡፡

12

ምሽትም ላይ አይጧ ፍየሎቹን ወደ ቤት ይዛ ገባች፡፡ ''ምን ነካሽ አይጡት?'' ሲል ነብሩ ጠየቃት፡፡ ''ዓይኖችሽ ምነው ደም መሰሉ?'' ''ዛሬ መድሐኒት አዋቂውን ጠርቼው ነበር'' አለችው አይጧ፡፡ ''ዓይኔ ላይ የማደርገው መድሐኒት ሰጥቶኝ ነው፡፡ መድሐኒቱም ዓይኖቼን ያሳድግልኛል፡፡ በደንብም አያለሁ፡፡''

13

ነብሩም ''እኔም ስለምፈልግ ምናለ ትንሽ ብትሰጪኝ ከመድሐኒቱ?'' አላት፡፡ ''እሺ'' አለች አይጧ፡፡ ''ግን ዓይኖችህን ሊያምህ ስለሚችል ላይስማማህ ይችል ይሆናል'' አለችው፡፡ ''አሁን ስጪኝ መድሐኒቱን'' አላት ነብሩ፡፡ ተኝቶም ዓይኖቹን በለጠጠ፡፡

14

አይጧ እሳት ላይ ድንጋይ ታግል ጀመር፡፡ ድንጋዮቹም አጋም መሰሉላት፡፡

15

ነብሩ ዓይን ላይም አደረገቻቸው፡፡ ''ድንጋዮችሽን አንሺልኝ!'' በማለት ነብሩ ጮኸ፡፡ ''ዓይኖቼን መልሺልኝ!'' አላት፡፡ ''እናቴን ስታመጣልኝ ዓይኖችህን እመልስልሃለሁ'' ብላ አይጧ በእፎይታ ተነፈሰች፡፡

16
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ነብርና አይጥ
Author - Abdulkadir Guracha, Elizabeth Laird
Translation - መዘምር ግርማ
Illustration - Rob Owen
Language - Amharic
Level - First paragraphs