የዲያብሎስ የአንገት ልብስ
Azeb Worku Sibane
Jacob Kono

ለረጅም ጊዜ ሚስት ሲፈልግ የነበረ አንድ ሀብታም ሰው ነበር፡፡ ሚስት አግኝቶ ሲያገባም አዛውንቶች የሰርጉን ስነስርዓት ባርከውለት ነበር፡፡

1

ለአንድ ዓመት ከሚስቱ ጋር ከኖረ በኋላ ልጅ ባለመውለዳቸው ይጨነቁ ጀመር፡፡ ሴትዮዋም ልጅ እንድትወልድ አዘውትራ ትጸልይ ነበር፡፡ ቢሆንም ግን ማርገዝ አልቻለችም፡፡

2

ልጅ የምትወልድበትን ቀን መጠበቁ ሰልችቷት አንድ ቀን ''ዲያብሎስዬ፣ ልጅ ከሰጠኸኝ ቆንጆ የአንገት ልብስ አሰራልሃለሁ'' አለች፡፡ በቀጣዩም ወር አረገዘች፡፡ ደስ ተሰኝታም ስለነበር ቃል የገባችውን የአንገት ልብስ አሰራች፡፡

3

ወንድ ልጅም ወለደች፡፡ ሁሉም ሰው የደስታዋ ተካፋይ ሆነ፡፡  የአንገት ልብሱን  ለዲያብሎስ ለመስጠት ብትፈልግም እሱን የማግኛውን መንገድ ግን አላወቀችውም፡፡ ስለሆነም አንድ አዛውንት ጋ ሄዳ ጠየቀች፡፡

4

አዛውንቱም ''ዲያብሎስን ለማግኘት ወደ ቤተክርስቲያኑ ሂጂ፡፡ ሁለት የተጣሉ ሰዎች አንድ ብልህ ሰውዬ ጋ ቆመው ታገኛለሽ፡፡ አልታረቅም ብሎ በንዴት የሚሄደው ሰውዬ ዲያብሎስ ነው! ለሱ የአንገት ልብሱን ስጪው!'' አሏት፡፡

5

ሴትዮዋም ወደ ቤተክርስቲያኑ ሄደች፡፡ ሁለት ሰዎች ከብልሁ ሰውዬ ፊት ቆመው አየች፡፡ ብልሁም ሰውዬ ''በቃ! አሁን ከልባችሁ ይቅር መባባያችሁ ነው'' ሲሏቸው፤ አንደኛው ሰውዬ ይቅርታ ለመጠየቅ ጎንበስ አለ፡፡ ሌላኛው ግን ''አልፈልግም'' ብሎ ሄደ፡፡

6

ሴትዮዋም ጠራችውና ''ጠብቀኝ! የምሰጥህ ነገር አለ'' አለችው፡፡ የአንገት ልብሱንም ሰጠችው፡፡ ሰውዬውም ተናዶ ''ምንድነው ይሄ?'' በማለት ጠየቃት፡፡ ሴትዮዋም ''ስጦታ ነው'' አለችው፡፡ እርሱም ''አልገባኝም፤ ይህን ስጦታ የምትሰጪኝ ለምንድነው?'' በማለት ጠየቃት፡፡

7

ሴትዮዋም ታሪኩን ነገረችውና ''አንተ አልታረቅም ያልከው ሰውዬ ስለሆንክ ዲያብሎስ ነህ ማለት ነው'' ብላ የአንገት ልብሱን ለመስጠት እጇን ዘረጋችለት፡፡

8

በዚህም ጊዜ ሰውዬው ወደ ቤተክርስቲያኑ ሮጠ፡፡ የተጣላውም ሰውዬ ጋ ሄዶ ተንበረረከና ''ምሬሃለሁ ወንድሜ፤ አንተም ማረኝ'' በማለት ተማጸነው፡፡ ያንኛውም ሰውዬ ተንበረረከከና ተቃቀፉ፡፡

9

ሴትዮዋም ዲያብሎስን እንደገና መፈለግ ጀምራለች፡፡ አደራ! የአንገት ልብሱ ግን ለእርስዎ እንዳይሰጥዎ ይጠንቀቁ፡፡

10
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
የዲያብሎስ የአንገት ልብስ
Author - Azeb Worku Sibane
Translation - መዘምር ግርማ
Illustration - Jacob Kono
Language - Amharic
Level - First paragraphs